አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የከፈተውን ወረራ ለማክሸፍ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ገለጸ።

253
ባሕር ዳር: ነሐሴ12/2013 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የከተቱ ምልምል ሰልጣኞች የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ዝግጁ እንደሆኑ የማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ አስታውቀዋል።
ምልምል ሰልጣኞቹ በማዕከሉ የሚሰጣቸውን ልዩ ልዩ ስልጠናዎች በከፍተኛ ሞራል እና ፅኑ በሆነ ሀገራዊ ፍቅር እየተከታተሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የከፈተውን ወረራ ለማክሸፍ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሰልጣኞች የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል ሁለገብ ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የሽብርተኛ ቡድኑ ወረራ ለመቀልበስ ምልምል ሰልጣኙም ኾነ የማዕከሉ ሠራዊት የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ማዕከሉ ከወቅታዊ ሀገራዊ ግዳጅ አንፃር የሚሰጠውን ልዩ ልዩ ተልዕኮዎች በአመርቂ ውጤት እየፈፀመ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
አንዳንድ የማዕከሉ አሰልጣኞች በበኩላቸው ሀገርን ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ ላይ አኩሪ ገድል መፈፀም የሚችሉ ብቁ ወታደሮችን ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ለመቅረፅ በትኩረት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ምልምል ሰልጣኞች የሽብር ቡድኑን ተግባር ለመመከትም ሆነ በሀገራችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ እስከ ህይወት መስዋእትነት ድረስ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የተዘነጋው የማይካድራ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እውነታው ሲገለጥ” ጋዜጠኛና ጸሐፊ ጀፍ ፒርስ
Next articleSudan can’t be credible party to facilitate negotiation: Expert