
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ፍሎሪዳ ጃክሰንቪልና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ 67 ሺህ 908 ዶላር ድጋፍ አሰባስበዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለተደረገው ድጋፍ እና ድጋፉን በማስተባበር ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በዕቅዳቸው ለማሰባሰብ ያሰቡትን 100ሺ ዶላር እንደሚያሳኩ እምነታቸውን መሆኑን እንደገለጹ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ