አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ባገናዘበ መንገድ የአሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ጥፋት የሚያጋልጥ ምላሽ መስጠት እንደሚገባት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

511

ባሕር ዳር: ነሐሴ11/2013ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ጄፋሪ ፊልትማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ምክትል ጠቅላይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሁለቱን ሀገሮች ረዥም ታሪካዊና በጋራ ጥቅሞችና ዕይታ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አውስተዋል።

አቶ ደመቀ የአሸባሪው ሕወሓት ወራሪ ኀይል በሰሜን ዕዝ ላይ ከፈጸመው ጥቃት ጀምሮ አሁን ያለበትን ዝርዝር ሁኔታን አስረድተዋል። በአሁኑ ሰዓት ወራሪው ቡድን በአማራና አፋር ክልል ግልፅ ወረራ፣ ዘረፋ፣ ግድያና ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥፋቶችን እያካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሸባሪ ቡድኑ ይህን ሁሉ ጥፋትና የሀገር ክህደት እየፈፀመ የአሜሪካ መንግሥት ድርጊቱን በሚመጥን ደረጃ እንዲሁም የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ባገናዘበ መንገድ የአሸባሪ ቡድኑን ጥፋት የሚያጋልጥ ምላሽ መስጠት እንደሚገባና ገንቢ ሚና እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያን ከማፍረስ ጀምሮ ቀጣናውን የሚያናጋ መሆኑ ሊሰመርበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አምባሳደር ጄፋሪ ፊልትማን በበኩላቸው የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕወሓት ላይ ያለውን አመለካከት በውል እንደሚረዱ ገልጸዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላት ፖሊሲ መሠረቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሰላም እና አንድነት በማስጠበቁ፣ በማረጋገጡ እና በማስቀጠሉ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሠረታዊ መልህቆች ላይ ተመስርቶ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ቀጣናዊ ትርጉም ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደር ጄፋሪ ፊልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

የመረጃ ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article32 የአሻባሪው ህወሓት ተላላኪዎች በቁጥጥር ሰር ዋሉ።
Next articleእኛም በድል ተወልደን፣ ክብራችሁን እናስጠብቃለን!