ፌዴራል ፖሊስ በአሸባሪው ቡድን የተያዙ ስትራቴጂክ ቦታዎችን ማስለቀቁን አስታወቀ።

689
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን የወረራቸው ስትራቴጂክ ቦታዎችን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ማስለቀቁን አስታውቋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ቆቦ ከተማን በመቆጣጠር ወደ ሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች በቀላሉ ለማለፍ በተለምዶ የአርሴማ ተራሮች የተባሉ አራት ተራሮችን ተቆጣጥሮ ለቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
ሆኖም የፌዴራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን አራት ፈጥኖ ደራሽ አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ የአሸባሪውን ኀይል በመደምሰስ አራቱንም ተራሮች በአንድ ቀን በማስለቀቅ ለአካባቢው ሚሊሺያ ማስረከብ እንደቻሉ ተገልጿል፡፡
የጠላትን ግብዓተ መሬት ሳንፈጽም አንመለስም ያሉት የሰሜን ዳይሬክቶሬት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ኢንስፔክተር ሀሰን አብዱ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን የትህነግ ቡድን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የተማመነባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች አስለቅቋል ብለዋል።
በዚህም የሽብር ቡድኑን ጀሌዎች በመደምሰስ ለአካባቢው ማኅበረሰብ መረጋጋት መፍጠር መቻሉን ነው የገለጹት።
አባላቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ሌላ ግዳጅ ለመሰማራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ትእዛዝ እየተጠባበቁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይም አሸባሪውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ዝግጁ መሆናቸውን የፈጥኖ ደራሽ አባላቱ ተናግረዋል።
ጦርነት የገጠምነው ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ እንደገና ወረራ ከፈፀመ ኀይል ጋር በመሆኑ ተራራ ሲይዝ ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ተራራ ሲለቅ “ተሸነፈ” ብለን ሳንዘናጋና ሳንደናገጥ ተልዕኳችንን በብቃት መወጣት ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ለሀገር ሉዓላዊነት ሲባል ህዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍና ጁንታውን እስከመጨረሻው ለማጥፋት መስዋእትነትም ጭምር ለመክፈል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል። ምንጭ: የፌድራል ፓሊስ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ ተናገሩ።
Next article32 የአሻባሪው ህወሓት ተላላኪዎች በቁጥጥር ሰር ዋሉ።