
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በሕልውና ትግል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መላው ኢትዮጵያውያንም አቅማቸው በፈቀደ መጠን በየአቅጣጫው ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡ በተለይ ባለሀብቶችና የንግዱ ማኅበረሰብ ታሪክ የማይረሳው ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስረድተዋል፡፡ ለዚህም ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ የንግድ ተቋማት ምንም አይነት ምጣኔ ሀብታዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይሕም ወቅቱን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ያለ አግባብ ለመበልጸግ ከመሻት የመጣ እንደሆነ ነው ርእሰ መሥተዳድሩ ያነሱት፡፡
‹‹የአማራ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ገጥሞት ይሕንን አደጋ ለመቀልበስ ትግል እያደረገ ባለበት በዚህ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ልቦና እንዲሰጣቸው መምከር እፈልጋለሁ›› ነው ያሉት፡፡
በዚህ ወቅት በሸቀጥና አገልግሎት ላይ ዋጋ ጨምሮ ገንዘብ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት ነውር መሆኑን አንስተዋል፡፡ በሕጋዊ መንገድ የሚደረገው ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ድርጊት የተሠማሩ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል ፡፡
ዘጋቢ፡-ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ