“በየአካባቢው የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎችን ነቅቶ መጠበቅ ግዴታችን ነው” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች

106
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ወጣት አይሸሽም አድማሱ ወጣቶች ሰርጎ ገቦችን በንቃት ሊከታተሉ እንደሚገባ ተናግሯል። የሚጠረጠሩ ሰዎችን ካየ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንደሚያደርግ ነው ወጣቱ የገለጸው። የሐሰት ወሬ በመንዛት ሽብር ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርግ ካለ በተደራጀ መልኩ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገባ ወጣት አይሸሽም ገልጿል። በግንባር ለተሰለፈው የወገን ጦር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነም ተናግሯል።
ወይዘሮ ዓየሁሽ ግድይሁን በአካባቢያቸው ያልተለመደ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ አካላትን ከተመለከቱ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንደሚያደርጉም ነው የተናገሩት።
ወጣቶች ተደራጅተው በየአካባቢያቸው የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎችን ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በግንባር ጠላትን እየተፋለመ ለሚገኘው የወገን ጦር ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ወይዘሮ ዓየሁሽ አሸባሪ ቡድኑ እንዲደመሰስ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
ወጣት ሙሉጌታ ሻምበል ኅብረተሰቡ ጸጉረ ልውጦችን ካስተዋለ ጥቆማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።
“እኔ የባጃጅ አሽከርካሪ ነኝ፤ በተለያዩ አካባቢዎች እንቀሳቀሳለሁ ተጠርጣሪዎችን ከተመለከትኩ ለመጠቆም ዝግጁ ነኝ” ብሏል። በህልውና ዘመቻውም በግንባር በመሰለፍ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ወጣት ጌትሽ ሙሳ ኅብረተሰቡ ከወትሮው በተለየ በማስተዋል መጓዝ አለበት ብሏል። “የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎች እንደ አበደ ውሻ በየቦታው ስለተበታተኑ አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል” ነው ያለው።
አካባቢያቸውን ለመጠበቅ አደረጃጀት መፍጠራቸውንም ጠቁሟል።
“በየአካባቢው የተበታተኑ የአሸባሪው ትርፍራፊዎችን ሳያጠፉን ነቅተን መጠበቅ ግዴታችን ነው” ብሏል። በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው የወገን ጦር አስፈላጊዉን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ሕዝባዊ ጦርነት ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን የወረታ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next articleየምዕራብ ጎንደር ዞን ሕዝብ በማይጠብሪ ግንባር ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን በመፋለም ለሚገኙ የጸጥታ ኀይሎች ድጋፍ አደረጉ።