የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ሕዝባዊ ጦርነት ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን የወረታ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

498
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚችለውን ንብረት በመዝረፍ የማይችለውን ደግሞ አውድሟል። ንጹሃን ዜግችን ደግሞ እየገደለ ይገኛል። ይህንን የህልውና አደጋ ለመመከት ጦርነቱ ሕዝባዊ እንዲሆን የክልሉ መንግሥት መግለጫ ሰጥቷል።
የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ ተቀብለው ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ነው በወረታ ከተማ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹት። ነዋሪዎቹ እንዳሉት አሸባሪው ትህነግ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለመበታተን ከውጭ ኀይሎች ጋር በመቀናጀት ዛሬም ባንዳነቱን አስመሥክሯል።
ይህንን ወረራ በጋራ መመከት ካልተቻለ እንደሌሎች ሀገራት እንደ ሀገር መቀጠል እንደማይቻል አንስተዋል። የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ በመቀበል ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለሠራዊት የሎጀስቲክስ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነግረውናል። የአማራ ሕዝብ በአሸባሪው ትህነግ መዳፍ ላለመውደቅ በሚካሄደው ትግል በሚችለው ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች እየሸሸ ያለውን የአሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ጦር መሣሪያ ይዘው ወጥተዋል።
Next article“በየአካባቢው የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎችን ነቅቶ መጠበቅ ግዴታችን ነው” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች