የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች እየሸሸ ያለውን የአሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ጦር መሣሪያ ይዘው ወጥተዋል።

238
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው፣ ተስፋፊው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች በሁሉም አካባቢዎች የጦር መሣሪያ ይዘው ወጥተዋል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የደባርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ ሙሉስሜ ሞላ እንደገለጹት ነዋሪዎች የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በመታጠቅ አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ተዘጋጅተው ወጥተዋል።
ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኃይሉ፣ ከሚሊሻ እና ፋኖ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው ብለዋል።
ወጣት ገብሬ ጌትነት ወጣቶች ተደራጅተው ሌት ተቀን አካባቢያቸውን እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግሯል። ጀግናው የደባርቅ ሕዝብ የሽብርተኛውን ትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በንቃት እየጠበቀ ነው ብሏል፡፡
የደባርቅ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ሰለሞን ተዘራ የከተማዋ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ከፍተኛ ጥበቃ እያደረጉ ነው ብለዋል። የጁንታው አባላት ሊገቡባቸው የሚችሉ ሁሉንም በሮች ዝግ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶችን ከጸጥታ ኀይሉ ጋር በማቀናጀት አካባቢውን እንዲጠበቁ እያደረጉ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ግንባር መሠለፍ ያለበትን አሰልፏል፤ የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ ያለበትን ደግሞ በሁሉም ኬላዎች አሠማርቷል ብለዋል። ጠላት ከገባም እንዳይወጣ ይደረጋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው-ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኦሮሚያ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ነፃነትን ያላንዳች መንገራገጭ ለማስቀጠል ዘብ መቆማቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
Next articleየክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን ሕዝባዊ ጦርነት ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን የወረታ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።