በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ የአፋር ልዩ ኀይል ገለጸ፡፡

166
በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ የአፋር ልዩ ኀይል ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር በአራት ወረዳዎች ወረራ ለመፈጸም ቢሞክርም የጸጥታው ኀይል የማያዳግም እርምጃ እየወሰደበት እንደሚገኝ የአፋር ልዩ ኀይል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር መሐመድ ሲራጅ ለፋብኮ ገልጸዋል።
የክልሉ ሕዝብ ከጸጥታው ኀይል ጎን ተሰልፎ አሸባሪውን ቡድን አደብ እያስገዛው ነውም ብለዋል ኮሚሽነር መሐመድ። ቡድኑ እየተሸመደመ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
በርካታ የአሸባሪው ቡድን አባላት መማረካቸውን ያነሱት ዋና አዛዡ ቡድኑ ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ጥሎ መፈርጠጡንም ተናግረዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየወሎ ላልይበላ የባሕል ቡድን በግንባር ተገኝቶ ለሠራዊቱ የማነቃቂያ ዝግጅት እያቀረበ ነው።
Next articleትውልዱ የአደራ ቃሉን በድል ይወጣል!