
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሀገር መከታ የሆነው ሠራዊት እያበረታቱ መሆናቸውን ስንዘግብ መቆዬታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የወሎ ላልይበላ የባሕል ቡድን በወሎ ግንባር ሠራዊቱን እያበረታታ ነው። ከወሎ ላልይበላ የኪነት ቡድን በተጨማሪ ካቤናት ኢትዮጵያ እና ውብ ኢትዮጵያ መልቲ ሚዲያዎች ከአዲስ አበባ በጎ ፈቃደኛ ድምፃዊያንንና የውዝዋዜ ባለሙያዎችን አስመጥተዋል።
ድምፃዊያኑና ተወዛዋዦችም ሠራዊቱን እያበረታቱ ነው።
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ ሠራዊቱ የመጨረሻውን ድል እስኪያጣጥም ድረስ ከጎኑ እንደማይለዩም አረጋግጠዋል።
ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ ነው፣ ሁሉም የኪነጥበብ ባለሙያ ሠራዊቱን ሊያበረታታ ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ