“ከግንባር ጠላት ሸሽቶ ሲወጣ ከቦ በመደምሰስ አንድም ጠላት እና በጠላት እጅ ያለ ንብረትና ትጥቅ እንዳይወጣ በማድረግ ማርከህ ያገኘኸውን ትጥቅ ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ” አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ

539

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መልዕክት
አስተላልፈዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
በጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል ፣ ፋኖ፣ ጀግና አርበኛ እና የደቡብ ጎንደር ሕዝብ በጋራ ጥምረት የሕዝባችን እና የሀገራችን አረሞች እየነቀለ እና ቀብራቸውን እያፋጠነ ይገኛል።
በሚያጋጥሙን ትንንሽ ችግሮች የተሸነፍን የሚመስለው የጠላት ኀይል እንደ እብድ ውሻ ሆኗል።
የእብድ ውሻ መጨረሻው ደግሞ ይታወቃል።
በሰሜን ወሎ በኩል ከወደ ወገልጤና አቅጣጫ እያጠቃ ባለወ የወገን ኃይል እስታይሽ ቀበሮ ሜዳ እና ጋሸና በቁጥጥራችን ስር ስለዋሉ ጠላት የስንቅ እና ትጥቅ እንዲሁም የሰው ኀይል በሩ ስለተዘጋ መፈርጠጡ አይቀሬ ስለሆነ የጋይንት፣ የጉና፣ የፋርጣ እና የእስቴ ነዋሪዎች እየሠራችሁት ያለው ገድል አይረሴ ነው እና እየከፈላችሁት ላለው መሰዋእትነት ከልብ የመነጨ ምስጋናየን አቀርባለሁ።
ከግንባር ጠላት ሸሽቶ ሲወጣ ከቦ በመደምሰስ አንድም ጠላት እና በጠላት እጅ ያለ ንብረትና ትጥቅ እንዳይወጣ በማድረግ ማርከህ ያገኘኸውን ትጥቅ ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ።
ወጥተህ ደምስስ!!
ታሪክን በደማቅ ቀለም ጻፍ!!

Previous articleበሶማሊ ክልል ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር በመፍጠር ሁከትና ግጭት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሸፈ፡፡
Next articleየወሎ ላልይበላ የባሕል ቡድን በግንባር ተገኝቶ ለሠራዊቱ የማነቃቂያ ዝግጅት እያቀረበ ነው።