
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በወሎ ግንባር እየተደረገ በሚገኘው አሸባሪውን ትህነግ የመደምሰስ ዘመቻ ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች በሥፍራው ተገኝተው እየሠሩ ነው። በወሎ ግንባር ያገኘናቸው በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ሀገርን የማዳን ተልእኮ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ አይደለም ብለዋል። የፖለቲካ ሰዎች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ እየሠሩ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
እንደ አንድ ግለሰብም አሸባሪው ትህነግን የማጥፋት ግዴታና ኃላፊነት አለብኝ ነው ያሉት። ወያኔ ወጣቶችን በሀሽሽ እያደነዘዘ እየላከ ነው፤ ብዙ የወያኔ ታጣቂ እየተደመመሰ ነው፤ የተሳካ ግዳጅ እየተደረገ ነውም ብለዋል። ሕዝቡም ልጆችን መርቆ እየላከ፣ ስንቅ እያቀበለና እየተዋጋ አስደናቂ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል። ጦርነቱ በአጭር ጊዜ አልቆ ወደ ሀገር ግንባታ እንደንመለስ እንፈልጋለን ነው ያሉት።
የሠራዊቱና የሕዝቡ ዝግጅት ትህነግን በአጭር ጊዜ ቀብሮ ሀገር ሰላም እንዲሆን የማድረግ አቅም እንዳለው መመልከታቸውንም ገልጸዋል። የሕዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ነው ያሉት።
ለሀገር ክብር ሲሉ ቤትና ንብረት ጥለው በግንባር ላይ ያሉ ሚሊሻዎችን የልማት ሥራ ሕዘቡ እንዲሠራም ጠይቀዋል።
የሸኔና የትህነግ ጋብቻ አዲስ አይደለም፤ ትህነግ መንግሥት ሆኖም ሳለ ኦሮሞን ለማተራመስ ሲፊልጉ ሸኔን ይመሩት እንደነበር ነው ያስታወሱት። ጋብቻቸው አዲስ አይደለም የቆዬ ነውም ብለዋል። የወያኔ እና ሸኔ ጥምረት ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል። ትህነግም ሸኔን በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸውም ነው ያሉት።
አሸባሪው ትህነግ በግንባር ጀግንነት እንደሌለው የገለጹት ዶክተር ዓለሙ የሚያሠራጨውን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። “ሁሉም ግዴታውን መወጣት አለበት፤ጠላታችን እስከንቀብር ድረስ ትግላችን መቀጠል አለበት” ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ