በሶማሊ ክልል ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር በመፍጠር ሁከትና ግጭት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሸፈ፡፡

197
በሶማሊ ክልል ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር በመፍጠር ሁከትና ግጭት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሸፈ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሶማሊ ክልል ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር በመፍጠር ሁከትና ግጭት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ በኅብረተሰቡና በጸጥታ አካላት የጋራ ጥምረት መክሸፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ሁከትና ግጭቱን ለማስነሳት ሙከራ ያደረጉት ኀይሎች በኢትዮጵያ ብሎም በሶማሊ ክልል የመጣው ለውጥ ጥቅማቸውን ያስቀረባቸው ኀይሎች ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ትስስር ፈጥረው እንደሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል።
አሸባሪው ሕወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የሶማሊ ክልል ሕዝብን አብረውት ሲዘርፉና ሲያዘርፉ የነበሩና ለውጥ ከመጣ በኋላ ከስልጣን የተወገዱ የቀድሞ አስተዳደር ርዝራዦች ከሕወሓት ተልዕኮ በመቀበል በክልሉ የሃይማኖት እና የጎሳ ግጭት በመፍጠር የከተማ ውስጥ አመፅ ለማቀጣጠል ሲሞክሩ እንደተደረሰባቸው ፖሊስ ጠቁሟል።
በሶማሊና በኦሮሞ መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርም አስታውቋል። ኢዜአ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ትህነግም ሸኔም በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸው” ዶክተር ዓለሙ ስሜ
Next article“ከግንባር ጠላት ሸሽቶ ሲወጣ ከቦ በመደምሰስ አንድም ጠላት እና በጠላት እጅ ያለ ንብረትና ትጥቅ እንዳይወጣ በማድረግ ማርከህ ያገኘኸውን ትጥቅ ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ” አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ