
የደብረታቦር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የሽብርተኛው ትህነግን ወረራ ለመከላከል የሚደረገውን ትግል እየደገፈ ነው።
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና ሲቪል ወዶ ዘማቾችን በሞራል እያበረታታ ወደ ግንባር በመላክ ላይ ነው።
ሕዝቡ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ላይ ነው። ጎን ለጎን ወጣቶች ድጋፍ ይሰበስባሉ፤ ውኃ፣ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ብስኩት እና ሌሎች ምግብና መጠጥ ገዝቶ መንገድ ላይ በመከዘን ለተጓዡ ሠራዊት እያደለ ነው። ጀግንነትን የሚያስታውሱ፣ ወኔ የሚሰንቁ፣ ድልን የሚያስናፍቁ፣ ቁጭትን የሚጭሩ፣ ስሜትን የሚፈጥሩ እልልታና ሆታ ፉከራ የሕዝቡ ለሠራዊቱ አቀባበልና አሸኛኘት የሚያደርግበት ስሜት ነው።
ዘጋቢ:— ዋሴ ባየ-ከደብረ ታቦር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m