“አሸባሪው የትህነግ ቡድን እንዲደመሰስ ለሠራዊታችን እያደረግን ያለው ድጋፍ አይቋረጥም” በደባርቅ ከተማ የሚኖሩ ሴቶች

189
ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደባርቅ ከተማ የሚኖሩ ሴቶች በጠለምት ግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ለሚገኘው የወገን ጦር የስንቅ ዝግጅት በማድረግ ደጀንነታቸውን አስቀጥለዋል፡፡
በስንቅ ዝግጅት ላይ ያገኘናቸው በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 የሴቶች ጉዳይ ኀላፊ ዓለምነሽ ስጦታው አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት እየተፋለመ ለሚገኘው ሠራዊታችን የደባርቅ ከተማ ሴቶች የተለያዬ አደረጃጀት ፈጥረው ድጋፍ በማድረግ የኋላ ደጀን መሆናቸውን አስቀጥለዋል ብለዋል፡፡
ከስንቅ ዝግጅት በተጨማሪም ሰርጎ ገቦችን የማደን ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኝ የተናገሩት ኀላፊዋ ሴቶች በጦር ግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለሙ እንደሚገኙም ኀላፊዋ ገልጸዋል፡፡
በህልውና ዘመቻው የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉን ደግሞ በስንቅ ዝግጅቱ እየተሳተፉ ያገኘናቸው የደባርቅ ከተማ ወጣቶች አስተባባሪ ወይዘሮ ዘይነብ መሐመድ ናቸው፡፡
ወይዘሮ ዘይነብ የሀገርና የሕዝብ አረም የሆነው የትህነግ አሸባሪ ቡድን እንዲደመሰስ ለሠራዊታችን የምናደርገውን የስንቅ ዝግጅት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ከስንቅ ዝግጅት ባለፈ በግንባር ተሰልፈው ጠላትን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸወንም ገልጸዋል፡፡
ለሠራዊቱ የስንቅ ዝግጅት ያለማቋረጥ እያከናወኑ መሆናቸውን የገለጸችው ወይዘሮ ሰላማዊት ወርቄ ናቸው፡፡
አሸባሪው ትህነግ ለሚነዛው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጡ ለሠራዊቱ ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በግንባር ተሰልፈው ጠላትን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ:- አድኖ ማርቆስ -ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ህልውናችንን ለማስጠበቅ ከሚያስፈልጉን ሥነ ልቦናዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ዝግጅቶች መሳ ለመሳ እየተደማመጡ የመሥራት ልምዳችንን ማጎለብት ያስፈልገናል❞ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
Next articleአሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬቱን በመፈፀም የኢትዮጵያን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ የሶማሊ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ።