
በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውኃ አካባቢ ተደምስሷል፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውኃ አካባቢ ተደምስሷል፡፡ በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ኀይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡
ጀግኖቹ የ21ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የድል ችቦዋቸውን ከፍ አድረገው እያውለበለቡ በጥቁር ውኃ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ መስራታቸውን ቀጥለዋል።
ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረውንና በከሃዲው ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራውን የጠላት ጦር በአስደናቂ የወታደራዊ ስልት መደምሰስ መቻሉን የ211ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ እና ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል አስታውቀዋል።
አዛዦቹ እንዳስታወቁት ፣ በሰራዊቱ እልህና ቁጭት አስደናቂ የጀግንነት ተግባር ፈፅመናል ብለዋል።
ክ/ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ ለይ በፈፀመው የጀግንነት ውሎው ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ፣ 19 ክላሽን ኮቭ መሣሪያ ፣ 5 ስናይፐር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል።
ሠራዊቱ አሁንም የህልውና ዘመቻውን በአስተማማኝ የጀግንነት መንፈስ ለመወጣት ከመቸውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ምንጭ: መከላከያ ሠራዊት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m