
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለም ወርቅ አሸባሪው ትህነግ ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች የእምነት ቦታዎችን፣ ተቋማትን እና የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን እንዳወደመ ገልጸዋል፡፡ አሸባሪው ቡድን ንጹሓን ዜጎችን ገሏል፤ የግለሰብም ሆነ የመንግሥት ንብረቶችን ባደራጀው ቡድን ዘርፏል ብለዋል፡፡
በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በጋይንት አካባቢ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው ቡድን በሀገር መከላከያ፣ በልዩ ኃይል፣ በሚሊሻ እና በፋኖ ጥምረት እየተደመሰሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ ነዋሪው ሕዝብም እሾህ ሆኖ እየወጋው ይገኛል ብለዋል፡፡
ሌሎች አካባቢዎችም እንደ ጋይንት እና አካባቢው ሕዝብ አሸባሪውን ትህነግ የደረሰበት ሁሉ መውጫ መግቢያ በማሳጣት መደምሰስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ