ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተት በመዘጋቱ የትራንስፖርት መስተጓጎል አጋጠመ፡፡

439
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተት በመዘጋቱ የትራንስፖርት መስተጓጎል አጋጠመ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተት ዓባይ በረሃ አካባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ በመዘጋቱ የትራንስፖርት መስተጓጎል ማጋጠሙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
ሌሊቱን ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል እንዳጋጠመ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።
ችግሩን በቶሎ ለመቅረፍም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ኃይል በመላክ በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ እየሠሩ እንደሆነ እና ሥራው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት ሲደረግ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሀገር ሊያፈርስ የተነሳውን አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ሁሉም በጋራ እንዲነሳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡
Next articleሕዝቡ አሸባሪው ትህነግን እሾህ ሆኖ እየወጋው እንደሚገኝ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ገለጹ፡፡