አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ወጣቶች እያደረጉ ያሉትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጥሪ አቀረበ፡፡

174
አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ወጣቶች እያደረጉ ያሉትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጥሪ አቀረበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሊጉ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አክሊሉ ታደሰ በመግለጫው ሽብርተኛው ትህነግ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ለማፍረስ መሥራቱን ተናግሯል፡፡
ሽብርተኛው ትህነግ ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ማዳከም ዋነኛ ዓላማዉ እንደነበርም አንስቷል። ሽብርተኛው ቡድን ሀገር እንድትፈርስ ጥረት ቢያደርግም በጀግኖች ልጆቿ እንዳልተሳካለት ነው ኀላፊው በመግለጫው ያነሳው፡፡
ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተከሰቱ መፈናቀሎች እና ወንጀሎች መሠረታቸው አሸባሪዉ ትህነግ ነው፤
ወጣቱ ይህን ተረድቶ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የተጠናከረ ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ወጣቶች እያደረጉ ያሉትነን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርቧል፡፡
በማይካድራ፣ በአፋር እና በሌሎች አካባቢዎች በአሸባሪዉ ትህነግ የደረሰዉን ጉዳት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት እንዳልሰጠዉም ጠቅሷል። የብልጽግና ወጣቶች ሊግ የቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
1. የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እሳቤ ምን እንደሚመስል ለወጣቱ ማሳወቅ፤ 2. የሽብርተኛው ትህነግን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ መመከት እና ከማስተጋባት መቆጠብ፤
3. ይህንን ጦርነት ለመመከት ከመዝመት ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ መሳተፍ፤
4. ወጣቱ አካባቢውን እንዲጠብቅ በማድረግ በቀጣዮቹ ሦስት ሳምንታት በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዉይይቶችን እንደሚያካሂድ እና ድጋፎችን ለማሰባሰብ እንደሚሠራም በመግለጫዉ አስታውቋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፣ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፣ ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዴሃን) የተሰጠ መግለጫ
Next articleሀገር ሊያፈርስ የተነሳውን አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ሁሉም በጋራ እንዲነሳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡