
ባሕር ዳር: ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው ቡድን ርዝራዦቹ ትናንት በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን የደረሠበትን አይቀጡ ቅጣት በመዘንጋት በሽብር ተግባር ዳግም የቅዠት ህልሙን አሣካለሁ ብሎ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቢሞክርም በጀግናው የ21ኛ ጉና ክፍለጦር የሠራዊት አባላት ሳንቃ በተባለው እና በጉባ ላፍቶ ወረዳ አካባቢ የሽብር ቡድን አባላትን ድባቅ በመምታት መደምሰስ ተችሏል ነው ያለው ክፍለ ጦሩ።
በሕዝቡ ጠንካራ የደጀን ደጋፍ አና በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ብርቱ ክንድ ኢትዮጵያን ለመበተን አፈር ልሼ እነሣለሁ ብሎ የሚፍጨረጨረውን ጁንታ ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም ሠራዊቱና ሕዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ቀን ከሌሊት ሳይሉ አሸባሪውን የሽንፈት ጽዋ እያስጎነጩት እንደሚገኝም አስታውቋል።
ትናንትም ዛሬም ለጠላቱ ግንባሩን የማያጥፈውጀግናው የ21ኛ ክፍለ ጦር ሠራዊት በሰሞነኛው የስኬትና የጀግንነት ውሎ በጭፍን ተነሳስቶና በከንቱ ህልም ተገፋፍቶ የሚገጥመውን እሳት በሚገባ ሳይረዳ የመጣውን አሸባሪ ቡድንና ባንዳ በመደምሰስ ታላቅ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን ገልጿል።
አሸባሪው ቡድን በሳንቃ፣ በጉባ ላፍቶና እንዲሁም በአራዶም ተራራና አካባቢው ጥቃት ለማድረስ አስቦ የነበረ ቢሆንም ጀግናው የ21ኛ ክፍለ ጦር አባላት በርካቶችን በመደምሰስ በርካታ የጦር መሣሪያ መማረክ መቻሉንም አመላክቷል።
አሸባሪ ቡድኑ ወልድያን ተቆጣጥሪያለሁ፣ ይህን ቦታ ይዣለሁ እያለ ሕዝብን የሚያሸብር ተግባሩን እንደ የአንድ የጦርነት ሥልት እየተጠቀመበት ነው መሆኑን የገለጸው ክፍለ ጦሩ ሕዝቡ በአሸባሪው ቡድን “የበሬ ወለደ” ወሬ ሳይደናገር ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ሕዝባዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቁን ከመከላከያ ሠራዊት ይፋዊ የማኅበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ