“ወቅቱ ሀገር የምናድንበት በመሆኑ ማንኛውንም መስዋእትነት መክፈል ጊዜው የሚጠይቅ ነው” የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባላት

142
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና አደጋ ለመፍታት ሥራውን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የቡድኑ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የሰላም ጥሪ ያልተቀበለ ቡድን ነው። አሸባሪ ቡድኑ እሰከ ሲኦልም ቢሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንታገላለን ማለቱ እብደት እንጅ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም ነው ያሉት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላቱ፡፡
የሽብር ቡድኑን ለመፋለም አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።
የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላቱ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን አደብ እንዲያስገዛ ጠይቋል፡፡
“ወቅቱ ሀገር የምናድንበት በመሆኑ ማንኛውንም መስዋእትነት መክፈል ጊዜው የሚጠይቅ ነው” ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን -ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በአሸባሪው ትህነግ ላይ ብርቱ ክንዳችንን እናሳርፍበታለን” የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ብርጌድ
Next articleመሸነፉ የማይቀርን ቡድን እድሜ ማራዘም እንደማይገባ የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከበደ ካሳ ተናገሩ።