የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ34ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመክፈቻ ሥነ‐ስርዓት እያካሄደ ነው።

488
የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ34ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመክፈቻ ሥነ‐ስርዓት እያካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሥነ ሥርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ፣ ሀገራችሁን በቅንነት ለማገልገል የውትድርና ሙያ በመምረጥ በሀገራችን የሚቃጣውን ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ፣ አሸባሪውን የጁንታ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ፣ ህዝብና ሃገርን ለመጠበቅ ጀግንነት የተሞላበት ውሳኔ ወስናችሁ እንኳን የጀግኖች መፍለቂያ ወደ ሆነው ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሰላም መጣችሁ ብለዋል።
ከምልምል ሰልጣኞች መካክል፣ አመሃ አሻግሬ እና ትግስት ሽበሽ በሰጡት አስተያየት፣ ውትድርና ሙያን ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደሚወዱትና ወታደር ለመሆን በመብቃቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። መረጃው የመከላከያ ሠራዊት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“እኛ ለማንነታችን ብንሞት ኩራት ነው፤ ወራሪ ያለቦታው ሲሞት ግን ውርደት ነው” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
Next articleየሰሜን ጎንደር ዞን የሥራ ኅላፊዎች አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ገለጹ፡