“ለአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የምንሰጠው ጊዜ አይኖርም” የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሠለ መሠረት

455
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ዕዝ ውስጥ የሚገኘውን 314ኛ ኮር 31ኛ ዓድዋ ክፍለ ጦር እና 54ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት እየወሰዱ ያሉትን ስልጠና እና ወትሮ ዝግጁነት የተመለከቱት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሠለ መሠረት አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከአሁን በኋላ በህይወት እንዲኖር አንፈቅድለትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሠራዊት አባላት እየወሰዱት ያለው ስልጠና አሸባሪውን የሕወሓት ቡድንን በአጭር ጊዜ መደምሰስ የሚያስችል እና ዳግም በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ የሚያደርግ ነው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን አሸባሪው የሕወሓት ቡድን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተቃወመው ይገኛል ያሉት ሜጀር ጀነራሉ ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ሠራዊቱ አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ ዘመቻውን እንዲያጠናቅቅ ስንቅ ይሆነዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት የፌዴራልና የክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
Next articleStatement on Current Affairs and a National Call from Prime Minister Office