የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ ለክብርና ለህልውና ዘመቻ የአርበኝነት ጥሪ አቀረቡ፡፡

641
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ ለክብርና ለህልውና ዘመቻ የአርበኝነት ጥሪ አቀረቡ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ዋና አስተዳዳሪው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሕዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት “ጀግንነትክን ሊፈትንህ ክብርህን ሊገፍህ ወራሪና ባንዳ ከደጃፍህ ደርሷል፤ ይህ ቡድን ባለፉት 50 ዓመታት አንተን ለማጥፋት ትግል ያደረገ ስለመሆኑ ለአንተ አይነገርህም” ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ሀገርን ሊያፈርስ እና አማራን ሊያንበረክክ ከውስጥና ከውጭ ባንዳዎች ጋር አንድ ሆኖ ሕዝብን መከራ ለማስከፈል ያለ የሌለ ኀይሉን ተጠቅሞ የሞት ሽረት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ባለፉት ቀናት ከሰሜን ወሎ ደጋማ አካባቢዎች ለማስወጣት ከፍተኛ አቅም እንዳለን ትናንት በጨጨሆ ግንባር በዋለው አውደ ውጊያ እንደታየ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት፣ ታች ጋይንት፣ ነፋስ መውጫ፣ ሰዴ ሙጃ፣ እብናት፣ ጉና በጌምድር እና መቀጠዋ ወረዳዎች የሚገኝ ትጥቅ ያለው አርበኛ ወደ ግንባር ተንቀሳቅሶ እየተፋለሙ ካሉ ወንድሞቹ ጋር በመሰለፍ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ደራ፣ ፎገራ፣ ሊቦ ከምከም፣ አንዳቤት፣ ፋርጣ፣ ደብረታቦር፣ ወረታ፣ መካነ ኢየሱስ፣ አዲስ ዘመን፣ እስቴ እና ስማዳ ትጥቅ ያለው ወገን በአደረጃጀቱ የግንባር ጥሪ እስኪደረግለት አካባቢውንና ሕዝቡን ነቅቶ እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ሁሉም ባለው የኀይል አደረጃጀት በመጠቀም፣ ከመሪዎች አመራር በመቀበል፣ የሚሠጠውን መመሪያ ብቻ በመፈጸምና ከዚህ ውጭ የሚሆን ኀይል ሲያጋጥምም ከአካባቢው መዋቅር ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡
“መሪዎችህ ከዘማች አርበኛቸው ጋር ጠላትን እየተፋለሙ ነው፤ መሪህ ግንባር ኾኖ አንተ ከቤትህ እንዳትውል፤ በፈጣሪ ስም ይዥሀለሁ” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው” የአሸባሪው ሕወሓት ምርኮኞች
Next articleየንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ለሠራዊቱ ስንቅ በማዘጋጀት ወደ ግንባር እያደረሱ ነው፡፡