
“ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው” የአሸባሪው ሕወሓት ምርኮኞች
ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2013 ዓ.ም(አሚኮ)”ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባና አፈና በዝቶብን ተሰቃይተን ነው” ሲሉ በአፋር ግንባር ተሰልፈው የነበሩ የአሸባሪው ሕወሓት ምርኮኞች ተናገሩ።
ካልአይ መምበረ በፈንቲ – ረሱ ግንባር በተካሄደው ውግያ ቆስሎ የተማረከ ሲሆን ከመቀሌ ከተማ ድንገት ታፍኖ ከታሰረ በኋላ የሦስት ቀናት ስልጠና ከተሰጣቸው መካከል አንዱ በመሆን ወደግንባር መምጣቱን ይናገራል።
በግንባር ሲገባም እሱን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ከመከላከያ ቀምተን እንሰጣችኋለን ብለዋቸው ያለመሳሪያ ወደ ጦርነት እንዳስገቧቸው ጠቅሶ ፤ በዚህ ሂደት ለማምለጥ ሲሞክርም ተመቶ መያዙን ነው የገለጸው።
“ወደ ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው” በማለትም ይናገራል።
ለአሸባሪው ቁንጮ አመራሮች የስልጣን ፍላጎት ማሳኪያ እድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ሕጻናትና ታዳጊዎችን በግፍ ወደ ለጦርነት እየማገዷቸው ነው።
ሌላው ምርኮኛ አንገሶም ገብረስላሴ በመቀሌ ከተማ በአሽከርካሪነት ከሚሠራበት በግድ ታፍኖ በመወሰድ መሳሪያ የመፍታትና መግጠም ስልጠና ብቻ ተሰጥቶት ወደ ጦርነት ተገዶ መግባቱን ተናግሯል።
ውጊያው እንደተጀመረም አብረውት የነበሩ በርካታ ሰዎች ሞተውና ቁስለኛ ሆነው ሲያይ ደንግጦ ህይወቱን ለማትረፍ ለመሸሽ ሲሞክር ተመቶ እንደተያዘ ነው ያስረዳው።
የመከላከያ ሠራዊትና የአፋር ልዩ ኀይል ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሰብዓዊነትና ወገናዊነት በተሞላበት መልኩ እንክብካቤና ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ጠቅሶ ለዚሀም ምስጋና አቅርቧል።
ምንም የማያውቁ ሲቪሎችና ታዳጊ ሕጻናት በግፍ ወደ ጦርነት እየተማገዱ በመሞት ላይ ስለሚገኙ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ በኋላ ለአሸባሪው መጠቀሚያ መሆን አይገባውም ብሏል።
ክብሮም ገብረማሪያም ሌላኛው ምርኮኛ ሲሆን ከመቀሌ ተይዞ በግዳጅ የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስዶ ወደጦርነት መግባቱን ተናግሯል።
አሸባሪው ቡድን የራሱን እድሜ ለማራዘም ክፉ ደጉን ያልለዩ የደሃ ትግራይዋን ሕጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች እየገፋ ወደ ጦርነት በማስገባት በአሰቃቂ ሁኔታ እያስፈጃቸው ነው።
የትግራይ ሕዝብ ለአሸባሪዎቹ የስልጣን መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆን በመቆጠብ ቡድኑን በቃህ ሊለው እንደሚገባም ወጣቶቹ አመልክተዋል። ኢዜአ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m