“በአሸባሪው የትህነግ ቡድን እየተካሄደ ያለው ወረራ፣ ጥቃት፣ ዘረፋና ግድያ ሁሉም በአንድነት ሊመክተውና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ኢትዮጵያን መታደግ ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን

630

በአፋር እና በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በአሸባሪው የትህነግ ቡድን እየተካሄደ ያለው ወረራ፣ ጥቃት፣ ዘረፋና ግድያ ሁሉም በአንድነት ሊመክተውና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ኢትዮጵያን መታደግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።

ባሕር ዳር: ነሐሴ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ቡድን እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በጋይንት ጨጨሆ አቅጣጫ በመቄት ወረዳ ደብረ ዘቢጥ አካባቢ የመስክ ጉብኝት አካሄዷል።

በጋይንት ጨጨሆ አቅጣጫ በመቄት ወረዳ ደብረ ዘቢጥ አካባቢ ወረራ፣ ጥቃት፣ ዘረፋና ግድያ እያካሄደ ያለውን አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመመከት የተሰለፈውን የመከላከያ ሠራዊት፣ የልዩ ኀይል፣ የሚሊሻ እና የፋኖ አደረጃጀት እንቅስቃሴ ቡድኑ በጉብኝቱ ተመልክቷል።

የአሸባሪውን ቡድን እኩይ እንቅስቃሴ እና ድርጊት ለመመከት ከጋይንት ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ
በከፍተኛ ወኔ እና ቁርጠኝነት የሚያደርገውን ጠንካራ ዝግጅት ቡድኑ ለመታዘብ ችሏል።

በየአከባቢው የሚገኘው ማኅበረሰብ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኀይሉ፣ ከሚሊሻ እና ከፋኖ ጋር በመቀናጀት ሀገርን የመታደግ ታሪካዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስደንቅ መሆኑን አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

የአካባቢው ማኅበረሰብ ለሠራዊቱ፣ ለልዩ ኀይሉ፣ ለሚሊሻው እና ለፋኖ አደረጃጀት ጠንካራ ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን በጉብኝቱ መታዘብ መቻላቸውን ገልጸዋል።

በአሁን ወቅት በአፋር እና በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአሸባሪው ቡድን እየተካሄደ ያለው ወረራ፣ ጥቃት፣ ዘረፋና ግድያ ሁሉም በአንድነት ሊመክተውና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ኢትዮጵያን መታደግ እንደሚገባ አቶ ደመቀ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“አብረን ወደ ፊት እንሄዳለን፤ አብረን የጀግንነት ሥራ እንሠራለን” ኮሎኔል አለበል አማረ
Next article“ሽብርተኛውን ቡድን ላይመለስ በመቅበር አንድነታችንን አጠንክረን መያዝ አለብን” የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው