
“አሸባሪው ህወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም”የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሐመድ
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ተናገሩ።
የሶማሌ ክልል በብርቆድ ወረዳ ሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ሚሊሺያዎችን አስመርቋል።
ርእሰ መስተዳድሩ አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሶማሌ ክልልን ለማተራመስ የተለያዩ ሴራዎችን እየሸረበ ቢሆንም አሸባሪው ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም ብለዋል። የለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሁሉም ዜጋ መታገል አለበት ገልጸዋል።
ለምረቃ የበቃቹት የሀገሪቱና የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ ስለሆነ በጎሳ ስም ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ሥራን የሚሠሩ ሰዎች መታገል አለባችሁ ብለዋል።



በሥነ ስርዓቱ ላይ የሶማሊ ክልል የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ እንደገለጹት የክልሉን ሰላም ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።
የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢንጀነር መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው ከለውጡ በኋላ እንደ ክልል ትላልቅ ድሎች እንደተመዘገቡ ገልጸው፣ ከድሎቹ መካከልም በክልሉ የሰፈነው አስተማማኝ ሰላም አንዱ እንደሆነገልጸዋለ።
ሰልጣኞቹ በስልጠና ወቅት የሀገርቱንና የክልሉን ሕገመንግሥት፣ የሰበዓዊ መብት አያያዝ፣ የመሣሪያ አጠቃቀምና ሌሎች ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን በክልሉ ወረዳዎች እንደሚመደቡ መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ