
ወልድያ እንደተለመደው በሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ቀጥላለች።
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ የሚያልማትና ተቆጣጠርኳት እያለ በተደጋጋሚ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጭባት ወልድያ ከተማ ዛሬም በሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ቀጥላለች። ሳያደርግ አደረኩ፣ ሳይዝ ያዝኩ እያለ የውሸት ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጨው አሸባሪው ትህነግ በሕዝብ በቁርጥ ቀን ልጆች እየተደመሰሰ ነው።
የከተማዋን እንቅስቃሴ በተመለከተ ለአሚኮ ሐሳባቸውን የሰጡት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ወልድያ ከተማ በተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ቀጥላለች ብለዋል። አሸባሪው ትህነግ በሚያስራጨው ሐሰተኛ ወሬዎች ወልድያ ከተማ ተይዛለች ቢልም ዛሬም ከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን ቀጥላለች ነው ያሉት።
ከተማዋ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዋን እንደ ወትሮው ሁሉ እያስሄደች ነው፣ ፍፁም ሰላማዊ ናት ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ በሚያሰራጨው ሐሰተኛ ወሬ መደናገጥ እንደማይገባም ተናግረዋል። ጠላት ምንጊዜም ጠላት ነው ያሉት ከንቲባው ማኅበረሰቡ በሐሰተኛ ወሬ ሳይፈታና ፊት ለፊት ጠላትን በመጋፈጥ አሸናፊ መሆን ይገባልም ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ በቅጥረኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎቹ አማካኝነት የሚያስዋራቸውን የውሸት ወሬዎች ማጋለጥና እውነቱን ለማኅበረሰቡ ማዳረስ ይገባልም ነው ያሉት።
በከተማዋ ምንም አይነት የተፈጠረ ነገር አለመኖሩን ያስገነዘቡት ከንቲባው የከተማዋ ነዋሪዎች የየዕለት ሕይወታቸውን እንደቀጠሉ ነው የተናገሩት፡፡
የወልድያ ከተማ ወጣቶች ተግባር እጅግ የሚመሰገን እና ከሚጠበቅባቸው በላይ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉ፣ ቆራጥ፣ ለሕይወታቸው ያልሳሱ ናቸውም ብለዋቸዋል። የከተማዋ ወጣቶች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ኾነው ጠላት ሰርጎ ሊገባባቸው የሚችሉ ቁልፍ ቦታዎችን በመጠበቅና ሰርጎ ገቦችን በመከታተል ረገድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ በመሥራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት ያለ ነውም ብለዋል። ጠላት የሚፈልገውን ነገር እንዳያደርግ እየተደረገ ስለመሆኑም ገልጸዋል።
ወጣቶቹ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ የሚመሰገንና ተጠናክሮ የሚቀጥል ነውም ብለዋል።
የከተማዋ ወጣቶች ከተማዋን ሌት ከቀን ከመጠበቅ ባለፈ በአውደ ውጊያ ላይም እየተሣተፉ ስለመኾናቸው ተናግረዋል።
የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ላያሸንፍ ሩጫ ጀምሯል፤ እንደሚሸነፍም ጠንቅቆ ያውቃል ያሉት ከንቲባው ቡድኑ እንዲደመሰስ ሕዝቡ በህልውና ዘመቻ ላይ የሚገኘውን ሠራዊት መደገፍና ማበረታታት እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።
አሸባሪው ትህነግ ሕዝቡን ከሠራዊቱ ለመነጠል እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። ሁሉም ማኅበረሰብ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ሠርጎ ገቦችን ማደን እንደሚገባውም አሳስበዋል።
በከተማዋ ለውጊያ ዝግጁ የኾኑ ወጣቶች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በማቀናጀት የማጥቃት ዘመቻውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመፈጸም ጠላትን ለመቅበር ተልእኮውን ወስዶ ዝግጁ የሆነ ማኅበረሰብ አለንም ብለዋል። ዝግጁ ከመሆንም በላይ አሁንም እየተዋደቀ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
