ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ሕይዎታቸውን ያጡ ሰማዕታት በሁመራ ከተማ እየታሰቡ ነው፡፡

252

ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ሕይዎታቸውን ያጡ ሰማዕታት በሁመራ ከተማ እየታሰቡ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 1/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” በሚል መሪ መልዕክት ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም በጠዋቱ ወጣቶች በባሕር ዳር ከተማ ጎዳናዎች የአማራን ሕዝብ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የማንነትና የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ አንግበው የተነሱ ወጣቶች ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ በነበረው ሕዝባዊ ሰልፍ መስዋእት ሆነዋል፤ በርካቶች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

የለውጡን ሰማዕታት ለመዘከር የባሕር ዳር ልዑካን አባላት በሁመራ ከተማ በጠዋቱ ችግኝ ተክለዋል። ወጣቶቹን ለመዘከር የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት፣ የአደራ ቃል ርክክብ እና ልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው ከሁመራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአንዳቤት ወረዳ ሚሊሻ አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ የሚካሄደውን የህልውና ዘመቻ ለመቀላቀል ወደ ግንባር አቀና፡፡
Next articleAmhara Fano, a command of the young people, of North Gondar Zone joins the survival campaign.