“ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ ግንባር እየደረሰ ነው” የሰሜን ግንባር የሎጅስቲክስ ግብረ ሃይል

137

“ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ ግንባር እየደረሰ ነው” የሰሜን ግንባር የሎጅስቲክስ ግብረ ሃይል

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈጸመውን ወረራ ለመመከት በግንባር ለተሠለፈው የጸጥታ ኀይል ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። የሚደረገውን ድጋፍም በአግባቡ እያደረሰ መሆኑን የሰሜን ግንባር የሎጅስቲክሰ ግብረ ሃይል ሰብሳቢ አንዳርጌ ዘነበ ገልጸዋል።

በሰሜን ግንባር ኦፕሬሽን ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰውን ድጋፍ በአግባቡ የሚያደርስ እና በሰሜን ጎንደር ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ የሚሰበስብ ግብረ ሃይል ተዋቅሮ እየተሠራ መሆኑን አቶ አንዳርጌ አስረድተዋል።

ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ለጸጥታ ኀይሉ የሚቀርበውን ድጋፍ ከጎንደር ማዕከላዊ ዕዝ በመረከብ በአግባቡ ወደ ግንባር የማድረስ ሥራ እየተሠራ ነውም ብለዋል ሰብሳቢው።

የህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉት ያለው ርብርብ በታሪክ ከፍ ብሎ ሊመዘገብ የሚችል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድርስ 3ሺህ 672 ካርቱን ብስኩት፣ 192 ኩንታል ስኳር፣ 323 ኬሻ በሶ፣ 327 ሰንጋ በሬ፣ 828 በግና ፍየል፣ ዳባ ቆሎ፤ ሽምብራ፣ ሳሙና እሽግ ውኃና ሌሎችም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ እየደረሱ መሆኑን አስረድተዋል። የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው–ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleThe Government of Ethiopia could not allow the warmongering group to launch new attacks in neighboring regions.: Ministry of foreign affairs of Ethiopia
Next articleወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!