
የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ አሰፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ ተናግረዋል፡፡
አሻባሪውን ትህነግ ለመቅበር የሚያስችል የሥነ አዕምሮም ኾነ ሁለንተናዊ ዝግጅት ተጠናቅቋል ነው ያሉት አቶ ቀለመወርቅ፡፡
ሽብርተኛው ቡድን በተለመደ የቅጥፈት እና የማወናበድ ተግባሩ ሕዝብን ለማሸበር እየጣረ መሆኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው “የአማራ ክልል ሕዝብ ላለፉት 30 ዓመታት የዚህን ቡድን የተንኮል ሴራ በደንብ ስለተረዳ በቡድኑ ውንብድና አይታለልም” ብለዋል፡፡
አቶ ቀለመወርቅ እንዳሉት በደቡብ ጎንደር ዞን ወጣቱ ተደራጅቶ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው የሚንሳቀሱ ተላላኪዎችን ተከታትሎ በመያዝ የቡድኑን የጥፋት ዓላማ በማክሸፍ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ የሚለቀቁ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ መረጃዎች ሳይሸበር የትህነግን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ እና ፋኖ የሚችለውን ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ ቀለመወርቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቢኒያም መስፍን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
