ኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነታቸውን የሚፈታተኑ ድርጊቶችን በምንም ሁኔታ እንደማይቀበሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡

124

ኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነታቸውን የሚፈታተኑ ድርጊቶችን በምንም ሁኔታ እንደማይቀበሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል። ኢትዮጵያዊያን በዘመናት የገጠሟቸውን ችግሮች አልፈው እንደ ሀገር የቀጠሉና ታሪክ የሠሩ ሕዝቦች ናቸው ብሏል የጋራ ምክር ቤቱ። የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ራሄል ባፌ (ዶክተር) የአምባገነንነት እና የመልካም አስተዳደር እጦት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደኋላ ጎትቷል ብለዋል።May be an image of 2 people, people sitting, people standing and indoor

አሸባሪው ትህነግ በመንግሥትነት ዘመኑ የኢትዮጵያዊያንን ሥነ ልቦና ከፋፍሎ ሲገዛ መቆየቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቀደሙት ጊዜያት በኮሪያ፣ በዩጋንዳ፣ በላይቤሪያ፣ በሶማሊያና አሁንም የጸጥታ ስጋት ባለባቸው ሀገራት መከላከያ ኀይሏን በመላክ ለሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለችም ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ።

“በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን የተሰለፋችሁ ወዳጆቻችንን እናመሰግናለን” ያሉት ፕሬዚዳንቷ አጋርነታቸውን እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። “ሀገራችንን ወደ አለመረጋጋት ውስጥ ለማስገባት ያለድካም የሚሠሩ ኀይሎች እንዳሉ እናውቃለን፤ ግን በድል እንሻገራለን” ያሉት ፕሬዚዳንቷ አሸባሪው ትህነግ በኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸም ወደጦርነት እንዲገባ ማድረጉን አስረድተዋል። የሀገር መከላከያ ጥቃት ደርሶበት አጸፋ የማይመልስ ሀገር የለም፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በበጎ መመልከት አለበት፤ ኢትዮጵያዊያን በሉዓላዊነታቸው የማይደራደሩና ለዚህም በህብረት የሚቆሙ መኾናቸውን መረዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።May be an image of one or more people, people sitting, people standing and indoor

ኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነታቸውን የሚፈታተኑ ድርጊቶችን በምንም ሁኔታ አይቀበሉም ያሉት ዶክተር ራሄል ኢትዮጵያ አሁንም የግዛት አንድነቷን ጠብቃ እንደምትዘልቅ አስረድተዋል፡፡

በቅርብም በሩቅም ያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የተናጠል ፍላጎታቸውን ለማሳካት እንደሚፈልጉ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ግን በሉዓላዊነታቸው አይደራደሩም፤ ይፈርሳሉ የሚሉትም የተሻገረችውን ዘመን እና የሠራችውን ታሪክ የማይገነዘቡ እንደኾኑ አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleብዙዎች ያወራሉ ወልድያዎች ይሠራሉ…
Next article“እንደቀድሞው ሁሉ የሚወደን ሰይፉን ይዞ ይከተለን” የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች