ማኅበረሰቡ ከሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የመከላከያ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

329
ማኅበረሰቡ ከሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የመከላከያ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው።
በአማራ ክልል በሙጃና ድልብ አካባቢ ሰርገው የገቡ የአሸባሪው ትህነግ ቡድኖችም እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አሸባሪው ትህነግ በአፋር በኩል ሰብዓዊና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበትም ነው የተናገሩት።
አሸባሪው ትህነግ ማይጠብሪ አካባቢ ባደረገውም ውጊያ የሞቱ የቡድኑ አባላትን በተከዜ ወንዝ ላይ በመጣል መከላከያ ያደረገው በማስመሰል የሐሰት ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ነው ብለዋል።
በራያ ቆቦና በአፋር አካባቢ አሸባሪው ቡድን የሚያደርገውን ወረራ ለማክሸፍ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህ ወቅት ካለው አሸባሪውን የመደምሰስ ተግባር በላይ ሐሰተኛ መረጃዎች አሳሳቢ ናቸዉ ያሉት ኮሎኔሉ ማኅበረሰቡ ከሚሰራጩ የአሸባሪው ቡድን ሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ -ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የደንብ ልብስ ለብሰው ከሚያጭበረብሩ አካላት ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ።
Next articleብዙዎች ያወራሉ ወልድያዎች ይሠራሉ…