
የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የደንብ ልብስ ለብሰው ከሚያጭበረብሩ አካላት ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ “ፖሊስ ወይም የጸጥታ አካላት ነን” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንጹሐን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የፌዴራል፣ የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው፣ ሐሰተኛ መረጃ ይዘው፣ ሕገ-ወጥ ብርበራና የዝርፊያ ሙከራ የሚፈጽሙ እንዳሉ ከሕዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጨማሪ መረጃዎችንም እንዳሰባሰበ ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስም በማሳሰቢያው መሰል ድርጊት የተፈፀመባችሁ ግለሰቦች ወይም በቀጣይ ከሕግና አሠራር ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥም ለፖሊስ አፋጣኝ ጥቆማ እንዲያቀርቡ ተጠይቋል።
ድርጊቱ ሕገ-ወጥ እንደሆነና በአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ቡድን ርዝራዦች ሊፈፀም እንደሚችልም ነው ፖሊስ ያሳሰበው።
ተመሳሳይ ድርጊት ሲያጋጥም ወደ ተቋሙ የስልክ መስመሮች ፈጥኖ በመደወል ሕገ-ወጥ ግለሰቦችን ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ለሚደረገው ጥረት የበኩላቹን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
ነፃ የስልክ መስመሮች 987፣ 816 እና 991, (አዲስ አበባ ፖሊስ)
ኢብኮ እንደዘገበው ለወንጀል መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077
ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የቢሮ ስልክ ቁጥሮች 0115309027፣ 0115309231 እና 0115309077
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቢሮ ስልክ ቁጥር 0111110111 ናቸው።
ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ሕግ የማስከበር ተግባር እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4
