“በሀገራችንና በሕዝባችን ህልውና በመጣብን ጠላት ላይ ምህረት የለሽ ክንዳችን አንስተን መታገል የሁላችንም ግዴታ ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

224

“በሀገራችንና በሕዝባችን ህልውና በመጣብን ጠላት ላይ ምህረት የለሽ ክንዳችን አንስተን መታገል የሁላችንም ግዴታ ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እንዳሉት በሀገራችንና በሕዝባችን ህልውና በመጣብን ጠላት ላይ ምህረት የለሽ ክንዳችን አንስተን መታገል የሁላችንም ግዴታ ነው።

“ወታደር የሌለው ሀገር እና አጥር የሌለው ቤት አንድ ናቸው፡፡ ሀገር ወዳድ ሠራዊት የገነባ ሕዝብ ሉዓላዊነቱ የተከበረ ሀገር ባለቤት ይሆናል፡፡ የቤቱን ቅጥር ግቢ በአጥሩ ያስከበረም እንዲሁ ተከብሮ ይኖራል” ብለዋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን የሀገራችንን ሠራዊት የማጥቃቱ ምክንያት አጥር አልባ ሀገርና ሕዝቦች ሊያደርገን አልሞ ስለመሆኑ ከቶውንም አልጠፋንም ያሉት አቶ ግዛቸው ለዚህም እንደ ሕዝብ የጠንካራ ሠራዊት ግንባታ ሥራ አካል በመሆን ሉዓላዊነቷ የማይደፈር ሀገር እና ጠላት የማይነቀንቀው አጥር እንዲገነባ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዛሬው የአውደውጊያ ውሎም በሳንቃ፣ በአለውኃ እና በሀራ ተወሽቆ የነበረው የአሸባሪው ቡድን በጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እና በጀግናው የወሎ ሕዝብ መደምሰሱን አስታውቀዋል።

ከአለውኃ ሸሽቶ ወደ ላልይበላና አካባቢው የፈረጠጠው የእሳት ራት የሆነው አሸባሪ ቡድንም እጣ ፋንታው ከዛሬዎቹ የእሳት ራቶች የተለየ አይሆንም ብለዋል።

በላልይበላ በኩል ውጊያ ሸሽቶ የገባው ቡድንም ከፊሉ እፈረጠጠ ለመውጣት እየሸሸ ሲሆን እንዳይወጣ ወጥመድ ተዘጋጅቶ ጀግኖቻችን በቅርብ እየተከታተሉት ይገኛሉ ነው ያሉት።

በሰሜን ጎንደርም የአሸባሪው ኃይል ተገቢውን ቅጣት እያገኘ እየተደመሰሰ እንደሚገኝ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በአሸባሪው ትህነግና በተላላኪዎች አሉቧልታ መረበሽ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።

በሁሉም አካባቢ የአሸባሪው ትህነግ ሰላዮችንና አስመሳይ ባንዳዎችን እንከታተል ያሉት አቶ ግዛቸው የወልድያ ወጣቶችን ጀግንነትና አይበገሬነት በሁሉም ቦታ ተግባራዊ እናድርግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4

Previous article“ድል ያለመስዋእትነት የማይታሰብ ነው” የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት
Next articleየፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የደንብ ልብስ ለብሰው ከሚያጭበረብሩ አካላት ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ።