በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡

175

በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴአቸው አማካኝነት ለአማራ ክልል የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኀይል በላኩት መልዕክት “እኛ እስራኤል ሀገር የምንኖር ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው ትህነግ የተቃጣውን ጦርነት ለመደምሰስ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኀይልና ለሚሊሻ፣ ፋኖ እንዲሁም ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሕግ ለማስከበር እና የሕዝብን ህይወት ከጥቃት ለመከላከል ለተሰማራዉ የጸጥታ ኀይል የሚዉል ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን አሸባሪው ትህነግ የፈጸመው ወረራ በእኛም ላይ የተቃጣ መሆኑን ተረድተን የአቅማችንን ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ በዚህም 8 ሺህ ዶላር በማሰባሰብ መላካቸውን የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ አምላኬ ዘለቀ ገልጸዋል፡፡

አሁንም በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን በመግለጽም እንዴት አሸባሪው ትህነግ ያጎረሰዉን ሕዝብ ለመዉጋት ይነሳል በማለት በቁጭት በመነሳሳት በድጋፉ በመሳተፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ መረጃውን ያደረሰን በእስራኤል ሀገር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ምዕራባውያን የሚመጡበት ምክንያት ከኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ፍላጎት ውጭ ከኾነ ሕዝብ እና መንግሥት ድርጊታቸውን ሊቃወሙ እንደሚገባ ምሁራን አስገነዘቡ፡፡
Next articleየአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር አልማ ከራያ ቆቦና ዋግኽምራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡