የሙሉዓለም የባህል ማዕከል በህልውና ዘመቻው ወቅቱን የሚመጥን ኹነት እያቀረበ ነው።

197
የሙሉዓለም የባህል ማዕከል በህልውና ዘመቻው ወቅቱን የሚመጥን ኹነት እያቀረበ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የባሕል አምባሳደር የኾነው የሙሉዓለም ባሕል ማዕከል በባለሙያዎቹ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በክልሉ መንግሥት የተደረገውን ጥሪ በመቀበል በየግንባሩ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኀይል፣ ለሚሻ፣ ለፋኖ፣ ለወጣቶችና ለየአካባቢው ኅብረተሠብ ወኔ ቀስቃሽ፣ሀገራዊ ስሜትና አንድነት የሚፈጥሩ የጥበብ ሥራዎችን እያቀረቡ ነው።
የሙሉዓለም ባሕል ማዕከል የባሕል ፕሮሞሽንና ፕሮግራሞች ዝግጅት ዳይሬክተር ሙላት ዋለ የባህል ቡድኑ “ዘመቻ ለህልውና የኪነ ጥበብ ዝግጅት” በሚል መሪ መልዕክት ለመከላከያ ሠራዊት፣ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ፣ለፋኖ እና ለሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ዝግጅቱን እያቀረበ ነው።
ዝግጅቱም የጸጥታው ኀይል በሀገራዊ ጉዳይ አንድ ላይ እንዲሰለፍ ለማድረግ እና ኅብረተሰቡም በአሸባሪው ትህነግ የውሸት ፕሮፖጋንዳ እንዳይደናገር ትክክለኛ መልዕክት ለማስተላለፍ የተካሄደ ነው ብለዋል።
የክልሉ የባሕል አምባሳደር የኾነው የሙለዓለም የባሕል ቡድን ኪነጥበብ ለልማት፣ ለሰላም፣ለህልውና ዘመቻና ለሌሎችም ሥራዎች ትልቅ አቅም ያለው መኾኑን በመረዳት ወደ ግንባር አቅንቶ ከጸጥታው ኅይል ጎን ተሰልፏል ነው ያሉት።
በጎንደር ከተማ፣ በዳባት ወረዳና በተለያዩ ግንባሮች በመገኘት ዘመናዊ እና ባህላዊ ሙዚቃ እና ትያትር በማቅረብ ሁሉም ሰው የጋራ ጠላትን በጋራ መመከት የሚያስችለውን የአንድነት መልዕክት እንዲያገኝ የማድረግ ሥራ መከናወኑን ነው የነገሩን።
“በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ወታደር ነው” ያሉት አቶ ሙላት የሙሉዓለም የኪነ ጥበብ አባላትም በቂ ዝግጅት በማድረግ ወቅቱን የሚመጥን ሁነት እያቀረቡ መሆኑን አብራርተዋል።
የሚቀርቡ ጭውውቶችና ቀረርቶዎችም ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚፈጥሩ እንደኾኑ የገለጹት አቶ ሙላት በህልውና ዘመቻው በአንድነት መቆም ካልተቻለ የመጣውን አደጋ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ይተርፋል ብለዋል።
“ዳሩን መቆጣጠር ካልተቻለ መሃሉም ዳር መኾኑ አይቀርም” ያሉት ዳይሬክተሩ ሁሉም ሰው ከመከላከያ ሠራዊት፣ከልዩ ኀይል እና ከፋኖ ጋር በመሠለፍ አሸባሪውን ትህነግ መደምሰስ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የኪነ ጥበብ ባለሙያውም የዘመተው ችግሩ የጋራ መኾኑን በመረዳት ነው ብለዋል። የገጠመው ችግር ለጸጥታው ኀይል ብቻ የሚተው ባለመኾኑ ኅብረተሰቡ በተለያዩ መንገዶች የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በአቀረቧቸው ወኔ ቀስቃሽ ዝግጅቶችም የጸጥታ ኀይሉ ሀገርን ለማዳን ከፍተኛ ወኔ ይዞ እየተጓዘ መኾኑን መገንዘባቸውን የነገሩን አቶ ሙላት ሁሉም ሰው ከአሉባልታና ከተሳሳተ መረጃ በመራቅ ባለው አቅምና ችሎታ ሀገሩን ማገልግል አለበት ብለዋል።
ዘጋቢ:- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“አሸባሪውን ቡድን ላይመለስ ሳንሸኝ እረፍትም፤ ምቾትም የለንም” አሸተ ደምለው
Next articleወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ምዕራባውያን የሚመጡበት ምክንያት ከኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ፍላጎት ውጭ ከኾነ ሕዝብ እና መንግሥት ድርጊታቸውን ሊቃወሙ እንደሚገባ ምሁራን አስገነዘቡ፡፡