የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ኀይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ ነው፡፡

133

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ኀይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ኀይል ለማመንጨት በሚችልበት ደረጃ መድረሱን የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።

በአማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች “አንድ እቅድ፤ አንድ ሪፖርት ለተቀናጀ የአባይ ተፋሰስ ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናት በባህርዳር ከተማ እያካሄዱ ነው።

በአውደ ጥናቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንዳሉት፤ ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ጽናት የታየበት ነው።May be an image of 10 people and people sitting

የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ሃይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱና ግንባታው ከ81 በመቶ በላይ መከናወኑ የዲፕሎማሲ የበላይነት እንድንጎናጸፍ ማስቻሉን አስታውቀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከ65 ሚሊየን ለሚበልጡ የሀገራችን ህዝብ መብራት ያስገኛል፤ የይቻላል መንፈስን ያዳበርንበት ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪካዊያን በፖለቲካው የተጎናጸፉትን ድል በኢኮኖሚው መስክ ለመድገም የሚያስችል በመሆኑ ከታቀደለት ጊዜ በላይ አገልግሎት እንዲሰጥ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

አርሶና አርብቶ አደሮች በተፋሰሱ ውስጥ እያከናወኑት ያለው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች በሳይንሳዊና በተግባር የተደገፈ ጥናት ዘዴ መደገፍ እንዳለበት አመልክተዋል።May be an image of ocean

ጽህፈት ቤታቸው በተፋሰሱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር በምርምር የተደገፈ የአፈር መከላትን በማስቀረት የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ዶክተር አረጋዊ ተናግረዋል።

ምሁራን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚካሄዱ ምርምሮችን ከተናጠል ይልቅ በጋራና በትብብር በመስራት ውጤታማና ችግር ፈቺ ለማድረግ ትኩረት እንዲሰጡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ በበኩላቸው፤ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀገራችን ከድህነት ለማላቀቅ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው” ብለዋል።

ግድቡ የኤሌክትሪክ መብራትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ፣ በገጠሩ አካባቢ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማስፋትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል።May be an image of 1 person and standing

“ታላቅ ነበርን ታላቅም እንሆናለን” የሚለው መሪ ሃሳብ በተግባር የሚረጋገጠው የህዳሴው ግድብ ዳር እስኪደርስ ምሁራን ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ለዚህም በክልሉ የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች በተፋሰሱ ዙሪያ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ሃብቱን አልምቶ ለመጠቀም የተግባር ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ አስማማው ቁሜ እንዳስረዱት፤ 28 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖረው በአባይ ተፋሰስ ነው።

ሀገሪቱ 45 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት ጠቁመው ከዚህ ውስጥ 17 ሺህ ሜጋ ዋት የሚሆነው አቅም የሚገኘው በአባይ ወንዝ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተፋሰሱን ስነ ምህዳር በመጠበቅና በወንዙ አጠቃቀም ላይ ሳይንሳዊ ሙግት በማካሄድ በወንዙና ገባሮች ላይ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን መደገፍ እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው አውደ ጥናት በተፋሰሱ ልማትና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያተኮሩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከወጣው መርሃ ግብሩ መረዳት ተችሏል። ዘገባው የኢዜአ ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ኀላፊዋ ሳማንታ ፓወር የኢትዮጵያ ጉብኝት ውጤታማ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“የገጠመን ሰይጣናዊ አሸባሪ ቡድን ነው፤ ሰይጣን የሚኖረው ደግሞ በደም ነውና በጋራ ልንዋጋው ይገባል” የ8ኛ መዓበል ሜካናይዝድ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ብርጋዲዬር ጀነራል ናስር አባዲጋ