አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 220 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

227

አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 220 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው እንዳሉትም የተመድ የእርዳታ እና የሰብዓዊ መብት ኀላፊ ማርቲን ግሪፍት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከተቋማት ኀላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል።

አቶ ደመቀ ከዚህ በፊት ተቋሙ ላደረገው እርዳታ በማመስገን ስለተናጠል ተኩስ አቁሙ እና ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ማድረስ ያልተቻለበትን ምክንያት አስረድተዋቸዋል ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ በከፈተው ጦርነት 220 ሺህ ሰዎች ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች መፈናቀላቸውን አቶ ደመቀ ያብራሩላቸው ሲሆን ይህን ተቋማቸው አለማውገዙ ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋቸዋል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።

ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይደርስ ያደረገው አሸባሪው ቡድን መሆኑን በመግለጽ በዚህ ወቅትም በአፋር ክልል ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደቦታው ሄደዋል ብለዋል።

ማርቲን ግሪፍት በበኩላቸው አሸባሪው ትህነግ እያደረገ ያለው አንቅስቃሴ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ለኢትዮጵያ የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ አቋማቸውን አሳውቀዋል ብለዋል አምባሳደር ዲና።

አቶ ደመቀ በበይነ መረብ ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መምከራቸውም ተብራርቷል።

ዘጋቢ:– አንዱዓለም መናን– ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleለህልውና ዘመቻው የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡
Next articleአሸባሪው ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ግፍ አስመልክቶ ያካሄደውን የጥናት ውጤት ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገለጸ፡፡