“ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትበታተናለች” የሚሉ አካላት እሳቤ የተሳሳተ መሆኑን የቀድሞ በኢትዮጵያ እና በጊኒ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ ገለጹ፡፡

240

“ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትበታተናለች” የሚሉ አካላት እሳቤ የተሳሳተ መሆኑን የቀድሞ በኢትዮጵያ እና በጊኒ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ቲቦር ናጊ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እና በጊኒ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ቀደም ሲል የአፍሪካ ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆንም ሠርተዋል፡፡ ቲቦር ናጊ በትዊተር ገፃቸው ባስተላፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የዘመናት ሀገረ መንግሥት ምስረታ ታሪክ ያላት ታላቅ ሀገር እንደሆነች አስገንዝበዋል፡፡

በርካታ ውጣ ውረዶችን ያለፈች ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል፡፡ በአንጻሩ ዩጎዝላቪያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች የተመሠረተች ሀገር እንደሆነች አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የገጠማትን አሁናዊ ችግር መነሻ በማድረግ ሁለቱን ሀገራት ፈጽሞ ማነጻጸር እንደማይቻል አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሰላሟን አረጋግጣ ወደ ነበረችበት ታላቅነቷ እንደምትመለስ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑ ባሮነስ አርሚንካ ሄሊች የተባለች ጸሐፊ “ፖለቲኮ ዩሮፕ” በተባለ እትም ኢትዮጵያን ከዩጎዝላቪያ ጋር አነጻጽራ መጻፏ ይታወሳል፡፡ ይህም የተሳሳተና በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሃቅ ያላገናዘበ መሆኑን በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያን በሚገባ የሚያውቁ ታዋቂ ሰዎች መረጃው ከሀቅ የራቀ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article”አሸባሪው ህወሓት ቀድሞም ህጻናትንና አረጋውያንን በጦር ግንባር የማሰለፍ አሳፋሪ ልምድ ያለው ቡድን ነው” ሜጀር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳ (አባ መላ)
Next articleለህልውና ዘመቻው የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡