የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ገለጹ።

687

የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ዛሬ ምሽት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ ቀደም ብለው በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ ከሰላም ሚኒስትርና ከሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በክልሉ የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ አሁንም መፋጠን እንዳለበት ጠቁመው በዚህም ከመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጋር መግባበት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።

ይሁንና በዚህ የሰብዓዊ ቀውስ ወቅት አሸባሪው ትህነግ ወደ አጎራባች ክልሎች የሚያካሂደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አንዳሳሰባቸው ነው ኀላፊዋ ሳማንታ ፓውር የተናገሩት።

በዚህ ትህነግ በሚያደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል 150 ሺህ ሰዎች በአፋር ደግሞ 76 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ነው ያረጋገጡት።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ላለፉት አራት ቀናት በሱዳን ጉብኝት አድርገዋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተግባር በመንቀሳቀስ በሀገር መከላከከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ጨምሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበኢትዮጵያ ክብርና ብሔራዊ ጥቅም ላይ የሚመጣን ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንደማይታገስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስገነዘበ።
Next articleየሕወሓት አሸባሪ ቡድን ሥርዓት የሚይዝ ከሆነ መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ እንደሚችል ገለጸ።