
“የትህነግ አሸባሪ ቡድን ካልጠፋ በስተቀር በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ሊኖር እንደማይችል አሜሪካ ልትገነዘብ ይገባል” የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትህነግ አሸባሪ ቡድን ካልጠፋ በስተቀር በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ሊኖር እንደማይችል አሜሪካ ልትገነዘብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ገለጸ።
የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅ ለእጅ ተያይዞ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች አሸንፋ እንድትሻገር የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት እየሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አምሳሉ ካሰው፤ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሱት ጫና የራስን ጥቅም ከማስጠበቅ የመነጨ እንጂ ለኢትዮጵያውያን አስበው እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
የምዕራባውያን ዋነኛ ፍላጎት በኢትዮጵያ ታዛዥ መንግሥት እንዲኖር መሆኑን ጠቅሰው፤ ነገር ግን በአሁን ላይ በኢትዮጵያ ያለው መንግሥት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለዜጎች ክብር የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት “ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራስን ችግር በራስ አቅም መፍታት” የሚል አዲስ እሳቤ ይዞ መምጣቱ ለምዕራባውያን ብዙም የተመቸ ሆኖ አልተገኘም ነው ያሉት።
ከዚህ አኳያ ምዕራባውያን የተቻላቸውን ጫና በማድረግ የኢትዮጵያን መንግሥት አቋም ማስቀየር እንደሚሹ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም መስፈን ከፍተኛ ሚና ያላት መሆኗን የገለጹት አቶ አምሳሉ፤ በኢትዮጵያ ላይ ጫና መፍጠር ቀጠናው እንዳይረጋጋ ያደርጋል ብለዋል።
በዓለም ጂኦ-ፖለቲካ ስትራቲጅክ ሚና ያለው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና አለመረጋጋት ከአፍሪካ በተጨማሪ ምዕራባውያንን እንደሚጎዳም መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
