ለህልውና ዘመቻው ተጨማሪ ተጠባባቂ ኀይል ማዘጋጀቱን የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

275

ለህልውና ዘመቻው ተጨማሪ ተጠባባቂ ኀይል ማዘጋጀቱን የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውን የትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ ጫፍ በአንድነት በመቆም ለህልውና ዘመቻው ድጋፉን እየሰጠ ነው። የአሸባሪው ክህደት የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ፍቅር የበለጠ ጎልቶ እንዲታይም አድርጓል፡፡

አካባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ የሚገኙ አሚኮ ያነጋገራቸው የቃብትያ ሁመራ ወረዳ የአዲህርድ ከተማ ሚሊሻ አባላት በአሸባሪው የትህነግ ቡድን እየተደረገ ያለውን ወረራ ለማስቆም እና በአካባቢው ሰርጎ ገቦች እንዳይኖሩ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የክተት ጥሪውን ተቀብላ ስልጠና ላይ የምትገኘው ወጣት አፀደ አክሊሉ “ሴትነቴ ወደ ግንባር ለመሄድ አያግደኝም” ብላለች። ወጣት አፀደ የአካባቢው ሴቶች እኔን ተከትለው የህልውና ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ከፊት ሆኘ እያነቃቃሁ እገኛለሁም ነው ያለችው።

“ለሀገሬ መስዋእት ለመሆን ዝግጁ ነኝ” ያለን ደግሞ ንጋቱ አስማረ ነው። ወጣት ንጋቱ አሸባሪውን የትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ እንቅልፍ ሊኖረን አይገባም፤ የተኛ ካለ ይንቃ ብሏል።

ወጣት ብርሃነ ጨርቆስ በበኩሉ “የአሸባሪው ቡድን መቀበሪያ አሁን ሊሆን ይገባል” ነው ያለው።

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳዳሪ ጌታሁን ሙሉ በአሁኑ ወቅት ከበቂ በላይ ኀይል ዝግጁ ኾኖ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ ወደ ግንባር ካሰማራናቸው የጸጥታ አካላት በተጨማሪ አካባቢያቸውን ከሰርጎ ገብ የሚጠብቁ አስፈላጊ ከሆነም ወደ ግንባር የሚዘምቱ ከበቂ በላይ ተጠባባቂ ኀይልን አሰልጥነን አዘጋጅተናል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ – ከአዲህርድ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪው ሕወሓት በታዳጊዎች ላይ የጦር ወንጀል እየፈጸመ መሆኑ ተገለጸ።
Next articleከአሰላ ከተማ የሀገር ጥሪ ተቀብለው የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ።