“ከወገን ጦር ጋር ጠላትን በመፋለም ህልውናችንን እናረጋግጣለን” የአዲአርቃይ ወረዳ ሚሊሻዎች

299

“ከወገን ጦር ጋር ጠላትን በመፋለም ህልውናችንን እናረጋግጣለን” የአዲአርቃይ ወረዳ ሚሊሻዎች

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲአርቃይ ወረዳ ሚሊሻዎች ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከሁሉም ክልል ከተውጣጡ ልዩ ኀይሎችና ፋኖ ጋር በመኾን የአሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ ላይ ይገኛሉ።

ሚሊሻ ጌታው ሙሉ አሸባሪው ቡድን መንግሥት ያደረገውን ተኩስ አቁም ተከትሎ በሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ ነው፤ ሀብት ንብረት እየዘረፈ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ ተስፋ በመቁረጡ ሀብት ንብረት እየዘረፈ ቢኾንም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል።

የአሸባሪ ቡድኑ አባላት የአርሶ አደሮችን የቤት እንስሳት፣ ቁሳቁስና እህል ወስደዋል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት ጠላትን ለመደምሰስ ሌት ከቀን፣ ዝናብና ውርጭ ሳይበግራቸው እየተፋለሙ እንደሚገኙም ነው የገለጹት።

“ከወገን ጦር ጋር ጠላትን በመፋለም ህልውናችንን እናረጋግጣለን” ለዚህም በቂ ዝግጅት አድርገናል ነው ያሉት።

እንደሽፍታ የሚንቀሳቀሰው አሽባሪ ቡድን የተዘራ ሰብል እያወደመ ነው፤ በሕዝብ ላይ ያለውን ጥላቻም ማሳየቱን ተናግረዋል።

ሌላው የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሙሉዬ መኳንንት እንደገለጹት አሸባሪው ቡድን ሀገር ለማፍረስ እየሠራ ነው ብለዋል።

አሽባሪው ይህን ቢያደርግም አማራው ከጥንት ጀምሮ የመንበርከክ ስሜት ስለሌለው ከወገን ጦር ጎን ተሠልፎ ልኩን እያሳየው መሆኑን አስረድተዋል።

ጁንታውን እስከ ወዲያኛው ለመሸኘት መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።

ዘጋቢ:- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ታሪክ ለማስተማር ሳይኾን ታሪክ ለመሥራት ወደ ግንባር እዘምታለሁ” በታሪክ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዲግሪ ምሩቅ መምህር ድምበሩ አለኸኝ
Next article“እነሱ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል ለመጓዝ ወደዋል፤ እኛ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመታደግ እነሱን እስከ ሲኦል ደጃፍ ድረስ ከመሸኘት አንዝልም” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ