ከተቋቋሙበት የሰብዓዊ ሥራ ዓላማ ውጭና የሀገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ታገዱ፡፡

325

ከተቋቋሙበት የሰብዓዊ ሥራ ዓላማ ውጭና የሀገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ታገዱ፡፡ከተቋቋሙበት የሰብዓዊ ሥራ ዓላማ ውጭና የሀገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ታገዱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ እንዳስታወቀው MSF HOLLAND፣
NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL እና AL MAKTOUME FOUNDATION የተባሉ የውጭ ድርጅቶች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ
የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች ከተቋቋሙበት የሰብዓዊ ሥራ ዓላማ ውጭና የሀገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ
ድርጅቶች ለሦስት ወራት ታግደዋል፡፡
MSF HOLLAND፣ NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL እና AL MAKTOUME FOUNDATION የተባሉ የውጭ
ድርጅቶች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰጣቸው ፍቃድ በሕጋዊነት በተለያዩ የሰብዓዊ ሥራዎች
ተሰማርተው እየሰሩ የቆዩ ድርጅቶች እንደነበሩ የጠቀሰው የመረጃ ማጣሪያው የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ ፍቃድ ሰጪው
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚያደርገው ክትትል መሰረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው
ነው የታገዱት ብሏል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
•አንደኛ- MSF HOLLAND እና NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL የተባሉ ድርጅቶች የተለያዩ ሐሰተኛ መረጃዎችን
በማኅበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ዘዴዎች ሲያሰራጩ በመገኘታቸው፣
•ሁለተኛ – ሦስቱም ድርጅቶች ስልጣን በተሰጠው አካል የሥራ ፍቃድ ያልተሰጣቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ
በማስገባት ከስድስት ወር በላይ ቀጥረው ሲያሠሩ በመገኘታቸው፤
•ሦስተኛ – MSF HOLLAND ድርጅት ስልጣን በተሰጠው አካል ፍቃድ ያልተሰጣቸው የሳተላይት የሬዲዬ መገናኛ መሳሪያዎችን
ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የድርጅቱ ሠራተኞች አፍራሽ ለሆኑ ዓላማ ሲጠቀሙበት እና ይዘው ሲንቀሳቀሱ በጸጥታ አካላት
ቀጥጥር ስር በመዋላቸው፣
•አራተኛ- AL MAKTOUME FOUNDATION የትምህርት ሚኒስቴር የኮሮናቫይረስ ፕሮቶኮልን ባለማክበር ፣ የበጀት አጠቃቀም
ግልጽነት የጎደለውና በትምህርት ቤት ስም የሚመጣን በጀት ከዓላማው ውጭ እየተጠቀመ በመሆኑ እንዲሁም በሠራተኞች
አስተዳደር ችግር የታየበት በመሆኑ ምክንያት ታግደዋል፡፡
ድርጅቶቹ ከተቋቋሙት ዓላማ ውጭና የሀገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ
ከድርጅቶቹ ኀላፊዎች ጋር ውይይት ቢደረግም ሊያስተካክሉ ስላልቻሉ አጠቃላይ ምርመራ ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ
ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 77(4) መሰረት አጠቃላይ የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ለሦስት ወራት የታገዱ መሆኑን
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ማሳወቁን ጠቅሶ የመረጃ ማጣሪያው በማኅበራዊ የትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ኢትዮጵያ የውጭ ኃይል ጣልቃ እንዲገባባት የማትፈቅድ ሀገር ናት” የቀድሞ የአሜሪካ የኮንግረስ እጩ አቶ ቴዎድሮስ ዓለማየሁ
Next article“ፖለቲኮ ዩሮፕ”ያወጣው ጽሑፍ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እንደማይገለጽ በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡