አሸባሪው ሕወሓት የዘረጋው ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ኔትዎርክ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

629

አሸባሪው ሕወሓት የዘረጋው ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ኔትዎርክ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሓት ከአዲስ አበባ እስከ ቶጎ ጫሌ በዘረጋው ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ እና የገንዘብ ዝውውር ኔትዎርክ፣ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ሰነዶች እና በርካታ ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

ዶላሩ ከአዲስ አበባ በጥቁር ገበያ እየሰበሰበ መንግሥትን እንዲዳከም ሲሠሩ የተደረሰባቸው መሆኑም ተገልጿል።

አሸባሪው ቡድን ቀድሞ በሠራው ኔትዎርክ በንግድ ተቋማት የሚሰበሰበውን የውጭ ምንዛሪ በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር እንዲወጣ በማድረግ ለሽብር ቡድኑ ዋነኛ የፋይናንስ ምንጭ መሆኑም ነው የተጠቆመው።

ፖሊስ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸውን ስድስት ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች፣ 11 ግለሰቦች ከ15 ባንኮች የተከፈቱ እና 10 ሚሊዮን 276 ሺህ 496 ብር፣ ከ100 በላይ የባንክ ደብተሮች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አሸባሪ ቡድኑ በአዲስ አበባ ሕጋዊ አሠራርን ሽፋን በማድረግ መንግሥት እንዲዳከም እና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገባቸው ጥሬ እቃዎች የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲያጋጥመው እንዲሁም የኑሮ ውድነትን አባብሶ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲነሳ ለማድረግ የሞከረ መሆኑንም ደርሼበታለው ብሏል ፌዴራል ፖሊስ።

በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪ ቡድኑ ደጋፊዎች ገንዘብ በመሰብሰብ ለጦር መሳሪያ ግዢ እና ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ወጪ ያውሉታል ተብሏል።

የሽብር ቡድኑ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠርም የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ማድረጉም ተገልጿል። ኢብኮ እንደዘገበው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከጠላታችን ትህነግ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ እስከ መጨረሻው ከጎናችን እንድትሆኑ እጠይቃለሁ” የመከላከያ ሚኒስቴር የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ
Next article“ኢትዮጵያን ከአሁናዊ ችግሯ ለማውጣት ለሠራዊቱ ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት እና በመተባበር ሊሰራ ይገባል” ደበበ እሸቱ