“የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከጠላታችን ትህነግ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ እስከ መጨረሻው ከጎናችን እንድትሆኑ እጠይቃለሁ” የመከላከያ ሚኒስቴር የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ

242

“የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከጠላታችን ትህነግ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ እስከ መጨረሻው ከጎናችን እንድትሆኑ እጠይቃለሁ” የመከላከያ ሚኒስቴር የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በሚል መሪ መልዕክት በኦሮሞ አርቲስቶችና የኦሮም ባህል ማዕከል የተዘጋጀ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዲኤታ ብዙነሽ መሠረት በዚህ ወቅት እንዳሉት የኦሮሞ አርቲስቶች ደም በመለገስና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ በመዘጋጀቱ ምስጋና ይገባል። ይህ ጅማሮ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴር የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ እንደገለፁት አሸባሪው ትህነግ እርሱን ለመጠበቅ የቆመውን ሠራዊት በወጋበት ወቅት ሕዝባችን ለአደረገልን ሁሉ ድጋፍና አጋርነት በመከላከያ ሚኒስቴር ስም ምስጋና ይገባል ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ የሌለና ያልተደረገውን ሆነ ተደረገ በሚል የሚነዛውን ወሬ የኪነ ጥበባት ባለሙያዎች እስከ ግንባር ድረስ ለመዝመት በመዘጋጀታችሁ እናመሰግናለንም ብለዋል።

ከታሪካዊው ጠላታችን ጋር በምናደርገው ፍልሚያ እስከ መጨረሻው ከጎናችን እንድትሆኑ እጠይቃለሁ ብለዋል ጀነራል ቡልቲ፡፡

ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleʺላትችሏት አትነቅንቋት ላታስቆሟት አትጎትቷት”
Next articleአሸባሪው ሕወሓት የዘረጋው ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ኔትዎርክ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡