ለአጣዬ መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በለንደን ተካሄደ።

158
ለአጣዬ መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በለንደን ተካሄደ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድጋፍ ለአጣዬ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ያካሄዱት። በገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብሩ ላይ ከ1 ሽህ 300 በላይ የዳያስፖራ አባላት፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ የውጪ ዜጎች እንዲሁም ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡
“አጣዬ ጥልቅ የአንድነት ሥነልቦና ተምሳሌት”በሚል ነው መልዕክት ነው ዝግጅቱ የተከናወነው።
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት
ሁሉም ነገር የሚያምረው በሀገር እና ሀገር ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በታሪካችን የተለያዩ ችግሮችን
የተወጣነው በሕብረት እጅ ለእጅ ተያይዘን በመቆማችን ነው ብለዋል፡፡
አጣዬ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነትና የሥነልቦና ተምሳሌት ናት ያሉት አምባሳደር ተፈሪ የአጣዬ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለማቆየት በህይወቱና በንብረቱ ለከፈለው ዋጋ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም ድጋፉን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአጣዬ ሕዝብ ጎን በመቆም የወደመውን ከተማ መልሶ ለማቋቋም አጋርነታችሁን ማሳየታችሁ የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት የምታደርጉት ያልተቋረጠ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ሀገራችን ተረጋግታ ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ እንዳይሳካ ከውስጥም ከውጪም ጠላቶቻችን በግልጽ
የከፈቱብንን ጥቃት እና የሸረቡብን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ መንግሥት እና መላው ሕዝብ በአንድነት የቆሙበት ወቅት በመሆኑ በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ሰላም፣ ልማት እና ደኅንነት ከምንጊዜውም በላይ ነቅቶ የሚታገልበት ዘመን እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
የሕዝቡን የአንድነት ድርና ማግ ለመበተን የተከፈተብንን ጥቃት በጋራ ከቆምን የማናሸንፍበት ምንም ምክንያት የለም ያሉት አምባሰደር ተፈሪ በውጪ ሀገራት በሚገኙበት የፓርላማ ተወካዮች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አንዳንድ አካላት እና መገናኛ ብዙኃኑ የያዙትን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያርሙ ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ ትስስር ገጽ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ እያደረጉ ያለው ያልተቋረጠ የሀገሩን ጥቅም የማስገንዘብ ዘመቻ እና ስለሀገሩ ሉዓላዊነት የሚያሳየው ተቆርቋሪነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም ግብረኃይል አስተባባሪ አቶ ዘላለም ተሰማ በበኩላቸው ለሰው ልጅ ክብር በሌላቸው ጽንፈኛ ኃይሎች በአጣዬ ላይ የደረሰው ውድመት መላውን ዜጋ ያሳዘነና ያስደነገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
አጣዬን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል፡፡
ለመከላከያ ሠራዊት እና በየአካባቢው ሀገራቸውን ነቅተው እየጠበቁ ላሉ የጸጥታ አካላት በተመሳሳይ ያልተቋረጠ ድጋፋችንን ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ የመጠበቅ ኀላፊነት የሁላችንም ነው ያሉት አቶ ዘላለም በቀጣይነትም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን ለማገዝ የቶምቦላ እጣ ተዘጋጅቶ አሸናፊዎች ተለይተዋል፤ በዕለቱም የቶምቦላ ከፍተኛ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደተቻለ ከለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleወጣቶች ለህልውና ዘመቻው ስልጠና እየወሰዱ ነው፡፡
Next articleየእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለሕልውና ዘማቾች የስንቅ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡