
ወጣቶች ለህልውና ዘመቻው ስልጠና እየወሰዱ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአባቶችን ታሪክና ገድል ለመድገም፣ የሀገራቸውንና የሕዝባቸውን ክብር ለመጠበቅ ወጣቶች የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
የከተማ አስተዳደሩ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ወረታዉ አቡሃይ ወጣቶች የክተት ጥሪውን በመቀበል የአሸባሪውን ትህነግ ግብዓተ መሬት ለማፋጠን በየአካባቢያቸው መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ ነዉ ብለዋል። ስልጠናዉ በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ ነው ያሉት አቶ ወረታው ስልጠናው በምልስ ሠራዊትና ልምድ ባላቸዉ የወታደር አባላት እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙ አሰልጣኞች በበኩላቸዉ ወጣቶች አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ያላቸዉን ወኔና ቁጭት አድንቀዋል።
ሰልጣኞችም አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ በላቀ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዲስ ዓለማየሁ – ከጎንደር


ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
