
የዓባይ ተፋሰስ ልማት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የዓባይ ተፋሰስ ልማት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የክልሉን የጸጥታ መዋቅር ለማጠናከር የሚውል የወር ደሞዛቸውን ጨምሮ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል፡፡
በተጨማሪም ሠራተኞቹ በግንባር ለዘመቱ ኀይሎች የደም ልገሳና አስፈላጊ ከሆነ እስከ ግንባር ለመዝመት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
